ዕድር ኖርዌይ
ዕድር ኖርዌይ ዘር፣ ሃይማኖት፣ ጎሳ፣ ቋንቋ፣ የፖለቲካ ድርጅት ሳይለይ ማንኛውም በኖርዊዌይ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣ ኤርትራዊያን እና ሌሎች ፈቃደኛ ዜጎች በአስቸጋሪ የህይወት ክስተቶች ውስጥ በቤተሰብ ወይም በቅርብ ዘመዶች መካከል የሞት አደጋ ሲያጋጥም በገንዘብም ሆነ በማህራዊ ትስስር እርስ በርስ ለመቆምና ለመደጋገፍ እንድንችል ታስቦ በሃገራችን ወግ፣ ባህልና ልማድ መሰረት ታስቦ የተቋቋመ የመረዳጃ ማህበር ነው። ማህበሩ በይፋ ከተቋቋመ ስድስት ወር የሆነው ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከመቶ በላይ አባላት አሉት። ስለዚህ ማንኛውም በኖርዊዌይ ውስጥ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣ ኤርትራዊያን እና ሌሎች ፈቃደኛ ዜጎች የዕድሩ አባል በመሆን ተጠቃሚ እንድትሆኑና እንዲሁም ሌላውን እንድትጠቅሙ ጥሪያችንን እያቀርብን ስለማህበሩ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ዋና ዋና ነጥቦችን በአጭሩ ለማስቀመጥ እንወዳለን።

