ዕድር ኖርዌይ

Publisert av Tadele Garedew Bahru den 15.01.26.

ዕድር ኖርዌይ በኖርዌይ ውስጥ ነዋሪ በሆኑ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን እንዲሁም ሌሎች ፈቃደኛ ዜጎችን በማሰባሰብ በሃገራችን ወግ፣ ልምድና ማህበራዊ እሴት መሰረት በዕድር ተደራጅተው ማህበራዊ ችግሮቻቸውን በተለይ የሞት አደጋ በሚደርስበት ወቀት በጋራ ተባብረው ችግሩን የሚወጡበትን መንገድ ለማዘጋጀት ታስቦ የተቋቋመ የመረዳጃ ማህበር (ዕድር) ነው። የዕድሩን ዝርዝር ዓላማና መተዳደሪያ ደንብ አሁን በመሰራት ላይ ባለው ይህ ድህረ ገጻችን ተደራሽ ለማድርግ እየሰራንበት እንገኛለን። እስከዚያው የማህበሩን አመራር በቀጥታ በሞባይል ወይንም ኢ-ሜይል እንዲሁም እዚሁ ድህረ ገጽ ላይ የሚገኘውን የመገናኛ መስመር (Kontaktskjema) በመጠቀም ጥያቄአችሁን፣ ሃስባችሁን እና አስተያየታችሁን እንድታጋሩን በማከበር እንጠይቃለን።