ዜና ዕረፍት

ወንድማችንና የማህበራችን አባል የሆኑት አቶ መስፍን ሃይሌ ባጋጠማቸው ድንገተኛ የጤና መታወክ ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሓሙስ ጥር 28 ቀን 2018 ዓ/ም (05.februar 2026) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ቤተሰባቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ጓደኞቻቸው እንዲሁም በርከት ያሉ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራዊያን በተገኙበት ሓሙስ የካቲት 5 ቀን 2018 ዓ/ም (12.februar 2026) ሥርዓተ ቀብራቸው በኦስትረ ግራቭሉንድ (Østregravlund) በክብር ተፈጽሟል።

አቶ መስፍን ሃይሌ በሕይወት በነበሩበት ወቅት ትሁት፣ ሰው አክባሪ፣ ስራ ወዳድና በተለይ በቤ/ክ አገልግሎት ከፍተኛ አስተዋጽዖ በማድረግ ላይ የነበሩ ሲሆን ለዕድራችንም ምስረታም የበኩላቸውን አስተውጽዖ አድርገዋል።

የዕድራችን የሥራ አመራር ኮሚቴ በማህበሩ አባላት ስም የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ይመኛል።