Gnist የራስ አገልግሎት ፖርታል (Mine sider)
ዕድር ኖርዌይ የሂሳብ አያያዝ ፣ የአባልነት ምዝገባ ፣ የድህረ ገጽ ፣ የራስ በራስ አገልግሎት ፖርታል (Gnist) ፣ ወዘተ ጨምሮ በማህበራችን አስተዳደር ውስጥ የ StyreWeb ን ሲስተም ይጠቀማል።
ማለትም StyreWeb ለዕድራችን የተሟላ የዘመናዊ ቴክኒኦሎጂ አገልግሎት መፍትሄ አቅራቢያችን ነው ማለት ነው። በዚህ መሰረት የዕድር ኖርዌይ አባላት Gnist APP መጠቀም ይችላሉ።
Gnist እንደ የራስ አገልግሎት ፖርታል ወይም Mine sider ተደርጎ መታየት ይችላል። በ Gnist አማካኝነት በዕድር ኖርዌይ ውስጥ ተመዝግበው የሚገኙትን መረጃዎችዎን አጠቃላይ እይታ ማግኘት፣ መለወጥ እና መከታተል ይችላሉ።
በGnist አማካኝነት አባላት ከማህበሩ ጋር የቀረበና የተቀናጀ ግንኙነት መፍጠር ይችላሉ። ከማህበሩ የሚመጡ መልዕክቶችንና እንቅስቃሴዎችን አጠቃላይ እይታ ይኖራቸዋል። እንዲሁም የራሳቸውን መረጃ ማዘመን እና ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ የመገለጫ ስዕል (Profilbilde) ማከል ይችላሉ።
አባላት እንዴት መጠወም ይችላሉ ወይንም እንዴት አክሰስ ያገኛሉ?
የተመዘገበ የኢሜል አድራሻ ያላቸው ሁሉም አባላት Gnist APP መጠቀም ይችላሉ። ለመጀመሪያ ጊዜ መጠቀም እንዲችሉ invitasjon lenk ከበቂ መረጃ ጋር እንልካለን ።
Gnist APP የሚጠቀሙ ከሆነ ለማህበሩ ቅርብ ነዎት፣ እና Gnistን እንደ "የእርስዎ ገጽ" አድርገው ማሰብ ይችላሉ።
• መረጃዎችዎን ወቅታዊ ማድረግ ይችላሉ
• የራስዎን የመገለጫ ስዕል (profilbilde) ማስቀመጥ ይችላሉ
• ከዕድር ኖርዌይ የሚላኩ መልዕክቶችን በቀላሉ መከታተል ይችላሉ
• የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች አጠቃላይ እይታ ይኖርዎታል
• ጥያቄ በቀጥታ ወደ ዕድር ኖርዌይ መላክ ይችላሉ
• የክፍያ መጠየቂያዎችዎንና ምን ያህል ክፍያ እንደፈጸሙ አጠቃላይ እይታ ይኖርዎታል
Gnist በሞባይል፣ ታብሌት እና ፒሲ/ማክ ላይ መጠቀም ይቻላል። የሞባይል መተግበሪያ ለሁለቱም አይፎን እና አንድሮይድ ተመቻችቷል። በዚህ ምክንያት አባላት ስለ ዕድር ኖርዌይ አስፈላጊ መረጃዎችን በሙሉ በኪሳቸው ውስጥ እንዳላቸው ይቆጠራል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ከላይ ሜኑ ላይ በተቀመጠው ኮንታክት ሼማ ያግኙን።
Gnist selvbetjeningsportal (min side)
EDER Norway benytter StyreWeb i foreningsdriften, og som del av dette har alle medlemmer tilgang til Gnist.
Gnist anses som en selvbetjeningsportal eller Mine sider. På Gnist kan du få full oversikt over dine opplysninger, endre og holde styr på dine informasjoner i EDER Norway.
Med Gnist kommer medlemmene tettere på foreningen. Her har de full oversikt over relevante aktiviteter og meldinger fra foreningen. De kan også oppdatere sine egne opplysninger og blant annet legge inn profilbilde.
Hvordan får medlemmene tilgang?
Alle medlemmer med registrert e-post adresse kan ta i bruk Gnist. Vi sender ut invitasjon til medlemmene med tilstrekkelig nok informasjon for å sete seg i gang.
Med Gnist er du tett på foreningen, og du kan tenke på Gnist som "Din side".
· Hold dine kontaktopplysninger oppdatert
· Legge inn ditt eget profilbilde
· Se meldinger fra EDER Norway
· Oversikt over aktiviteter
· Skriv en henvendelse direkte til EDER Norway
. Se oversikt over dine fakturaer
Gnist kan benyttes både på mobil, nettbrett og PC/Mac.
App for mobil er tilpasset både for iPhone og Android.
App på mobiltelefon er tilpasset både for iPhone og Android. På denne måten sørger vi for at medlemmene har alt av nødvendige informasjon om EDER Norway i lomma!