ዕድር ኖርዌይ አጠቃላይ ስብሰባውን ሰኞ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ/ም (06. april 2026) አካሄደ። በዲጂታል(Zoom) በተካሄደው ስብሰባ ላይ በርከት ያሉ በተለያዩ የኖርዌይ ከተሞች የሚገኙ ነባርና አዳዲስ አባላት ተሳትፈዋል።
በስብሰባው ላይ የስራ አመራር ኮሚቴው የሥራ እንቅስቃሴና የሂሳብ ሪፖርት ያቀረበ ሲሆን በተሻሻለው ሕገ ደንብ ላይም ሰፊ ማብራሪያ ተስጥቷል። እንዲሁም ከአባላት በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ውይይት ተድርጓል።
የስራ አመራር ኮሚቴውን በጸሃፊነት የሚያገለግል አንድ አባል እንዲመረጥ ኮሚቴው ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ወ/ሮ ብሩክታይት አሉላ ከ Nordland fylke, Bodø ኮሚዩን ዕድሩን በጸሃፊነት ለማገልገል ፈቃደኛነታቸውን ገልጸዋል። በዚሁ መሰረት ለሚቅጥሉት ዓመታት ወ/ሮ ብሩክታይት አሉላ የዕድሩ ጸሃፊ ሆነው ያገለግላሉ። መልካም የአገልግሎት ዘመን እንዲሆንላቸው እንመኛለን።